ከነገ ጀምሮ በሚቀየረው የአንበሳ እና ሸገር አውቶቡሶች የመገልገያ ትኬት የዋጋ ጭማሪ አልተደረገም ተባለ

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት የአንበሳና ሸገር ከተማ አውቶቡሶች የመገልገያ ትኬት ዋጋ በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን ጣቢያችን ሰምቷል

የአዲስ አበባ አውቶብስ አገልግሎት ድርጂት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ሳሙኤል ፍሰሃ ለጣቢያችን እንደገለፁት የትኬቶቹ መቀየር ከዚህ በፊት በሁለቱ ባስ ትኬት ልዩነት የተነሳ የህዝቡን ግራ መጋባትን ሙሉ በሙሉ የሚያስቆምና አገልግሎት እንዲቀላጠፍ የሚረዳ ነው ብለዋል

በተጨማሪም በታሪፉ ጉዳይ የሚደረግ ለውጥ ካለ የመዲናዋ የትራንስፖርት ቢሮ በኪሎ ሜትር ባወጣው ታሪፍ መሰረት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑንም ነግረውናል

በመሆኑም አውቶቡሶቹ ከዚህ ቀደም ሲጠቀሙበት የነበረው ትኬት በባለ 5፣ 10፣ 15፣ 20 እና ባለ 25 ብር ይቀይራል ተብሏል፡

በዚህም መሰረት የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በሁለቱም ድርጅቶች የተቀየረው አዲስ ቲኬት ሙሉ በሙሉ ሥራ እንደሚጀምር ተገልጿል

በመጨረሻም አቶ ሳሙኤል ከነገ ጀምሮ በሚደረገው በትኬት ቀለም ለውጥ ግራ መጋባት ካለ እንዲሁም በታሪፍ ላይ ማንኛውም የዋጋ ጭማሪ ሲያጋጥመው ማህበረሰቡ በ8981 ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ማሳወቅና መረዳት ይችላል ብለዋል

በልዑል ወልዴ

መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *