በትግራይ እየተፈፀሙ ላሉ ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች የአስተዳደሩ የፀጥታ እና ፍትህ ተቋማት ተገቢው ምላሽ እየሰጡ አይደለም በማለት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ተቋማት ተቹ።

እነዚህ በተለይም በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ተቋማት በጋራ በሰጡት መግለጫ በትግራይ አሳሳቢ የሆነው ፆታ መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት ያወጣው ያለፉት 11 ወራት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፥ በመቐለ ብቻ ባለፉት ወራት በ12 ሴቶች ላይ ግድያ የተፈፀመ ሲሆን 80 የአስገድዶ መድፈር ወንጀሎች መመዝገቡ ይገልፃል።

10 የእገታ ተግባራት፣ 178 የግድያ ሙከራ ወንጀሎች በመቐለ ባለፉት 11 ወራት መፈፀማቸው የመቐለ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

በመቐለ ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በተለይም በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታ መሰረት ያደረጉ ወንጀሎች መበራከታቸው በተለያዩ አካላት ይገለፃል።

በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ያሉ በሴቶች የሚደርሱ ጥቃቶች በማውገዝ ከሃያ አምስት በላይ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሲቪል ተቋማት በጋራ በሰጡት መግለጫ፥ ከጦርነቱ በኃላ ጭምር በትግራይ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ግፎች፣ ዓመፅ፣ ማገት እና መግደል በስፋት መቀጠላቸው አስታውቀዋል።

ሲቪል ተቋማቱ በትግራይ ያሉ የፍትህ እና ፀጥታ ተቋማት በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በመከላከል እና ተጠያቂነት በማረጋገጥ በኩል የሚጠበቅባቸውን ሐላፊነት እየተወጡ አይደለም በማለትም ወቅሰዋል።

ሐምሌ 02 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *