የሀገሪቷን የገቢ እና ወጪ ንግድ ያግዛል የተባለዉ ነፃ የንግድ ቀጠና የሎጀስቲክ እና የንግድ መሰረተ ልማት ስራን ማጠናቀቁን ሰምተናል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረኩት የድሬደዋ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ረሺድ ነፃ የንግድ ቀጠናዉ ስራ ለሀገራችን አዲስ ከመሆኑ አኳያ የአለማቀፍ ልምዶችን በተከተለ መልኩ መሰራቱን ገልፀዋል።
የዉስጥ መመሪያዎች እና ደንቦችም ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን የገለፁት አቶ አህመድ ነፃ የንግድ ቀጠናዉን በአዋጅ የመደገፍ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
በነፃ የንግድ ቀጠናዉ እስካሁን ከ300 በላይ የሀገር ዉስጥ ሆነ የዉጪ ኢንቨስተሮች እና አልሚዎች ተመዝግበዋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል በድሬደዋ ኢንደስትሪ ፓርክ ዉስጥ የነበሩ 6 ያህል ፋብሪካዎች በነፃ የንግድ ቀጠናዉ በስራ ላይ መሆናቸዉ ታዉቋል።
ነፃ የንግድ ቀጠናው አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ዉስጥ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሊገባ ስለመሆኑ ሰምተናል።
የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና በ2014 ዓ/ም ተመርቆ መከፈቱ ሚታወስ ነዉ።
በቁምነገር አየለ
ሐምሌ 04 ቀን 2016 ዓ.ም
