ከ4መቶ በላይ ሰዎች ከህልፈተ ህይወት በኋላ የአይን ብሌናቸውን  ለመለገስ ቃል ገብተዋል ተባለ

221 የአይን ብሌን በመሰብሰብ ለንቅለ ተከላ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉ ተነግሯል፡፡

ለቀዶ ጥገና ዝግጁ የሚሆን 255 የአይን ብሌን ለማሰባሰብ  እና ወደ ህክምና ተቋማት ለመላክ በእቅድ ተይዞ  221 የአይን ብሌን ተሰብስቦ  የምርመራ ስርዓት ውስጥ በማሳለፍ ለንቅለ ተከላ ዝግጁ እንዲሆን ማድረግ መቻሉን

የኢትዮጲያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ  አገልሎት ምክትል ዳይሪክቴር እና የአይን ባንክ አስተባባሪ ሀብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ 500 ሰዎች የአይን ብሌን ለመለገስ እቅድ ለማስያዝ ታቅዶ 456 የሚሆኑ ሰዎች የአይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህም ከታቀደው 91 በመቶ  ማሳካት መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

በ2015 በጀት ዓመት የአይን ብሌን ለመለገስ ቃል የገቡት 190 ሰዎች እንደሆኑ ያስታወሱ ሲሆን፤ የዘንድሮ በጀት ዓመት ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር መሻሻሎች መስታዋላቸውን  ተመላቷል፡፡

እሌኒ ግዛቸው

ሐምሌ 5 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *