የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት በራሳቸው ፈቃድ ኃላፊነታቸውን ለቀቁ፡፡

ሳውዝ ጌት ከፈረንጆቹ 2016 ጀምሮ የእግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል፡፡

በቡድኑ በነበራቸው ቆይታ በ2024ቱ እና 2021ዱ የአውሮፓ ዋንጫ እንግሊዝን ለፍጻሜ ማድረስ ችለዋል፡፡

እንዲሁም በ2018 የዓለም ዋንጫ እስከ ግማሽ ፍፃሜ እና በ2022 የዓለም ዋንጫ ደግሞ እስከ ሩብ ፍፃሜ አድረሰዋል፡፡
ይሁን እንጂ በቆይታቸው ዋንጫ ማሳካት ባለመቻላቸው ትችት ሲሰነዘርባቸው ቆይቷል፡፡

በመሆኑም ከስምንት ዓመታት በኋላም በይፋ ከብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝነታቸው መሰናበታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በ17ኛው የአውሮፓ ዋንጫ ለፍጻሜ የደረሰችው እንግሊዝ በስፔን 2 ለ 1 መሸነፏ ይታወሳል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *