የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ሃላፊ የሆኑት ጆሴ ቦሬል የተባበሩት መንግስታት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲን እንደ አሸባሪ ድርጅት መፈረጁን ህብረቱ ውድቅ እንዳደረገ ገልፀዋል።
ሃላፊው እንደ አሸባሪ ድርጅት ለመሰየም የሚደረገውን ማንኛውንም ሙከራ አንቀበልም ያሉ ሲሆን፤
በተጨማሪም እንዴት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ አሸባሪ ድርጅት ሊቆጠር ይችላል ሲሉ ድርጊቱን አውግዘዋል።
ሀላፊው ከዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አይማን ሳፋዲ ጋር በብራሰልስ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እቅዱ እንደማይሳካም አረጋግጠዋል።
አያይዘውም የአውሮፓ ህብረት ከሌሎች አለም አቀፍ ለጋሾች ጋር በመሆን ለእለት ደራሽ የምግብ አቅርቦት እና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡
በሊዲያ ደሳለኝ
ሐምሌ 09 ቀን 2016 ዓ.ም
