ንጉሱ የ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር የመጀመሪያ የህግ አውጭ ፕሮግራምን በማስቀመጥ ንግግሩን መስጠት ጀምሯል።
ወደ 35 የሚጠጉ ረቂቅ ፖሊሲዎችን ለማስታወቅ ንግግር እንደሚያደርጉ ተጠብቋል
1.5 ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት ብሔራዊ የቤት ግንባታ ፕሮግራምን፣ የባቡር ሀዲድ እና የሰራተኛ ቃል ኪዳንን በተጨማሪም የሰራተኞች መብት ህግን ጨምሮ 35 ረቂቅ ህጎችን ይዘረዝራል ተብሎ ይጠበቃል
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር ለሚቀጥሉት አመታት የመንግስት አጀንዳዎች ለማስተዋወቅ ተዘጋጅተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እርምጃዎቹ የኢኮኖሚ እድገትን በማፋጠን እና በአገሪቱ ላይ እና ታች ላሉ ሰዎች ሀብት ይፈጥራሉ ብለዋል ። እንደ አዲሱ የፖሊሲዎች ስብስብ፣ ሁሉም የመንግስት በጀቶች ነጻ ምርመራ እንዲደረግላቸው እና የአካባቢ መንግስታት ተጨማሪ ስልጣን እና ህግ ሊያገኙ ይችላሉ።
እንዲሁም የድንበር ደህንነትን ለማጠናከር አዳዲስ እርምጃዎች ይጠበቃሉ።
በቁምነገር አየለ
ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
