ሄዝቦላህ የሚሳኤል ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ዜጎች መጠለያ እንደሚፈልጉ ተገለጸ፡፡

ሄዝቦላህ የሚሳኤል ጥቃት ማዝነቡን ተከትሎ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ሰፋሪዎች ከሚሳኤል ጥቃት ለማምለጥ መጠለያ ፍለጋ ውስጥ እንደሆኑ ተናግረዋል።

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት ሄዝቦላህ በሜሮን፣ ናሃሪያ እና ሌሎች የመጠለያ ሰፈሮች ላይ ባደረሰዉ የሚሳኤል ጥቃት ከ60ሺህ በላይ የሚሆኑ እስራኤላዊያን ሰፋሪዎች በድንጋጤ ስፍራዉን ለቀዉ መዉጣታቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

ሄዝቦላህ 80 ሮኬቶችን ወደ እስራኤል የተኮሰዉ እስራኤል በቅርቡ በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት የሶስት ሶሪያዊያን ህጻናት ህይወት ማለፍን ተከትሎ የበቀል እርምጃ ለመዉሰድ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከባለፈዉ ጥቅምት ወር ጀምሮ ሁለቱም ወገኖች በሊባኖስ ደቡባዊ ድንበር በየዕለቱ በሚባል ደረጃ የተኩስ ልዉዉጥ ሲያደርጉ መቆየታቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የሄዝቦላህ ባለስልጣናት ከእስራኤል ጋር ጦርነት እንደማይፈልጉ ሲሉ ደጋግመው ሲናገሩ የቆዩ ቢሆንም ጦርነቱ ሊከሰት ግድ ከሆነ ግን ዝግጁ መሆናቸዉን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ ሲል ፕሬስ ቴሌቭዥን ዘግቧል፡፡

በሊዲያ ደሳለኝ

ሐምሌ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *