በአማራ ክልል በርካታ የታጣቂ ቡድን አባላት እና አመራሮች በመንግስት የቀረበላቸውን የሰላም አማራጭ ተቀብለው ሰላማዊ ሕይወት እየመሩ መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡
በትናንትው እለት በአማራ ክልል የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አሰግድ መኮንን ለመንግስት ፀጥታ ሃይሎች እጁን መስጠቱን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል አስታውቋል፡፡
ግለሰቡ እጁን የሰጠው በፅንፈኛ ሃይሉ አመራሮች እና ታጣቂ ቡድን አባላት አማካኝነት በአማራ ክልል ህዝብ ላይ የሚፈፀሙ አሰቃቂ ግድያዎች፣ እገታዎች፣ ለሕዝብ ጠቀሜታ የሚውሉ መሰረት ልማቶች ውድመት፣ አፈና እና ሌሎችም ኢሰበዓዊ ድርጊቶች እተበራከቱ በመምጣታቸው እንደሆን በሰጠው ቃል ማረጋገጡን መግለጫው ጠቁሟል፡፡
የፀጥታ እና ደህንነት የጋራ ግብረ ሃይል አክሎም ኮሎኔል አሰግድ መኮንን እጁን የሰጠው ከቅርብ አጃቢው ገበየሁ ወንድማገኝ ከተባለ የቡድኑ አባል ጋር መሆኑን ግብረ ሃይሉ አመልክቷል ።
የሰላም አመራጭን ተቀብለው ለሚመጡ የታጣቂ ቡድን አመራሮች እና አ ባላት ግብረ ኃይሉ የሚያደርገውን ድጋፋና ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል፡፡
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
