ኢራን በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ስትጓዝ የነበረችን ነዳጅ ጫኝ መርከብ በቁጥጥር ስር አዉላለች

የኢራን የባህር ሃይል በፐርሺያ ባህረ ሰላጤ ውስጥ በህገ ወጥ መልኩ ሲጎጎዝ የነበረ ከፍተኛ መጠን ያለው የነዳጅ ታንከር በቁጥጥር ስል ማዋሉን አስታዉቋል ፡፡

የህንድና የሲሪላንካ ዜግነት ያላቸው አስራ ሁለት ሰራተኞችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነው የተነገረዉ።

የባህር ሀይሉ በሰጠው መግለጫም የቶጎ ባንዲራ የያዘች መርከብ ከ1ነጥብ5 ሚሊዮን ሊትር በላይ ህገወጥ ነዳጅ ይዛ ሲሸጋገር ነበር ብሏል።

ነዳጁን ሲያሸጋግሩ የተገኙት በደቡባዊቷ የወደብ ከተማ ቡሻህር የባህር ዳርቻ ላይ ‘ቤልት ጉሴ’ በተባለች የነዳጅ መርከብ መሆኑ ተነግሯል፡፡

በጥር ወር መጨረሻ ላይ የኢራን የባህር ሃይል በደቡባዊ የውሃ ክፍል ሁለት ሚሊዮን ሊትር ህገ ወጥ ነዳጅ ጭና የነበረች መርከብ መያዙ ፕሬስ ቴሌቪዥን አስታዉሷል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *