የጎፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳግማዊ አየለ እንደገለፁት በመሬት ናዳው በአንድ የቤተሰብ አባላት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ እነሱን ለማትረፍ እና ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ ለነብስ አድን ሥራ ወደ ስፍራው ባቀኑ ሰዎች ላይ ተጨማሪ አደጋ በመድረሱ የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ችሏል።
በአደጋው ለነብስ አድን ሥራ ቀድመው በስፍራው የተገኙ የቀበሌውን አስተዳዳሪ
ጨምሮ መምህራን፣ የጤና ባለሞያዎች እና የግብርና ባለሞያወች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል።
እስካሁንም ከአደጋው በህይወት መውጣት የቻሉት 5 ሰዎች ብቻ መሆናቸውን ማወቅ ተችሏል።
የነብስ አድን ሥራ እየተከናወነ የሚገኘው በሰው ኃይል ብቻ በመሆኑ ለተጨማሪ የነብስ አድን ሥራ ድጋፍ እና ትኩረት ወደ ዞኑ እንዲሆን የዞኑ አስተዳዳሪ ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም
