የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማናገር ጥረት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጉዳዩን አስመልክቶ የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንን ለማግኘት ጥረት በማድረግ ላይ እንደሚገኝና ጉዳዩም በበጎ መልኩ እልባት እንደሚያገኝ ያለውን ዕምነት ገልጻል።

የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንበላከው ደብዳቤ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 30 ቀን 2024 ዓ.ም. ጀምሮ አየር መንገዳችን ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን ሁሉንም በረራ ማገዱን አሳውቆናል ብሏል ባወጣዉ አጭር መግለጫ።

በዚሁ አጋጣሚ አየር መንገዱ ተጨማሪ መረጃዎች እንደተገኙ ለውድ ደንበኞቹ እንደሚያሳውቅ አሳዉቋል፡፡

የኤርትራ የሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣንበጋዜጣ ላይ ባወጣው መግለጫ አየር መንገዱ እንዲታገድ የተወሰነው ያልተገባ የንግድ ተግባራት” በመከተሉ ነው ሲል ኩባንያውን ወቅሷል።

የኤርትራ መንግሥት ከዚህ ውሳኔ ከደረሰባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ በአየር መንገዱ ተጓዦች ላይ “የተደራጀ እና ስልታዊ የሻንጣ ስርቆት” ይፈጸማል የሚለው ይገኝበታል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት ወደ አሥመራ በሳምንት አምስት በረራዎችን ያደርጋል።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪ የሳዑዲ አረቢያ፣ የቱርክ እና የግብፅ አየር መንገዶች ወደ አሥመራ መደበኛ በረራዎችን አሏቸው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሐምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *