የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር መመሪያን እንደ ምክንያት በመውሰድ ያለተገባ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉና ምርትን ያለአግባብ ባከማቹ ከ700 በላይ የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸውንና 33 ነጋዴዎች ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ በመጨመር እና ምርትን ያለአግባብ ላከማቹ 1257 ድርጅቶች የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መሰጠቱንም ገልጸዋል።
የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር መመሪያን ተከትሎ በህብረተሰቡ ላይ ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መንግስት ተግባራዊ ያደረገውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ምክንያት በማድረግ በሸቀጦች ላይ አለአግባብና ወቅቱን ያላገናዘበ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና አለአግባብ ምርት ባከማቹ 71 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ_አህመድ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡን ተከትሎ ባልተገባ ሕገ ወጥ መንገድ ለመጠቀም በሚፈልጉ “ስግብግብ ነጋዴዎች” ላይ የሕግ አስፈጻሚ አካላት ርምጃ እንዲወስዱ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።
ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
