በሀረሪ ክልል 3411 የንግድ ሱቆች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነዉ ተባለ።

በመንግስት ይፋ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በሀረሪ ክልል 289 የንግድ ተቋማት እና ነጋዴዎች ላይ ማስጠንቀቂያ እንደሰጠ የክልሉ ኢንደስትሪ እና ልማት ቢሮ ሀላፊ እስማኤል የሱፍ ለአኢትዮ ኤፍኤም ገልፀዋል።

እስካሁን በክልሉ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ እና የምርት መደበቅ ተግባር በፈፀሙ 48 የንግድ ሱቆች መታሸጋቸዉ ታወቋል።

የዋጋ ጭማሪ እና ምርት በደበቁ 7 ያህል ግለሰቦችም ለፍርድ ማቅረብ እንደተቻለ ተናግረዋል።

ክልሉ በዋና ዋና ቦታዎች ላይ ያሉ የንግድ ተቋማት ለነጋዴዎች የዋጋ ዝርዝር በየሱቆቹ ዉስጥ መለጠፍን አስገዳጅ እንዳደረገ ታወቋል።

የምርት መጋዘኞች ላይ የምርት ክምችት እንዳይኖር  ከፍተኛ በሚባል መልኩ ቁጥጥር እና የህግ ክትትል ላይ ስለመሆናቸው ሀላፊዉ ገልፀዋል።

በርካታ ነጋዴዎች እቃዎችን ከድሬደዋ  ስለሚያመጡ ከዛ የሚደረግባቸዉ የዋጋ ጭማሪ አስመልክቶ ከድሬደዋ ከተማ ጋር ስራዎች እየተሰራ እንደሆነም አንስተዋል።

በክልሉ በተለያዩ ሸቀጦች ላይ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት ጭማሪ እንደሌለ እና  ነዋሪዎች መብታቸዉን የመጠየቅ ግዴታ ያለባቸዉ በመሆኑ ለቢሮዉ ጥቆማ እንዲያደርጉ ሀላፊዉ አሳስበዋል።

ቁምነገር አየለ

ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *