እስራኤል ለጦርነት ጊዜ ሊውል የሚችል ከምድር በታች ግዙፉ ሆስፒታል ማዘጋጀቷ ተሰምቷል

ሆስፒታሉ ከ2ሺህ በላይ አልጋዎች አሉት።

ለጊዜውም ቢሆን ግን ታካሚዎች የሉትም።

በሰሜናዊ እስራኤል በምትገኘው ሃይፋ ከተማ ከምድር በታች የሚገኘው ግዙፉ ሆስፒታል ለጦርነት ጊዜ እራሱን ማዘጋጀት መጀመሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ሆስፒታሉ በኮንክሪት ግንቡ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ አልጋዎችን የመያዝ አቅም አለው። ቀዶ ሕክምና ክፍሎች፣ የእናቶች ማዋለጃ ክፍል እና የመድሃኒት ማከማቻ መጋዘኖች አሉት።

ራምባም ሜዲካል ማዕከል ይህን ያስገነባው እአአ ከ2006ቱ የእስራኤል-ሄዝቦላ ጦርነት በኋላ ነበር።

ይህ ከምድር በታች በርካታ ወለሎች ያሉት ግንባታ በሰላማዊ ጊዜ ለመኪና ማቆያሚያነት የሚያገለግል ሲሆን ግንባታው የተከናወነው አስፈላጊ በሆነ ጊዜ በሦስት ቀናት ውስጥ ወደ ሆስፒታል እንዲቀየር ተደርጎ ነው።

መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ሐማስ እስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ከምድር በታች ያለው ወለል ወደ ሆስፒታልነት ለመቀየር በተጠንቀቅ ላይ ሆኖ ቆይቷል።

አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ማየሉን ተከትሎ መኪና ማቆሚያ ወደ ሆስፒታልነት እየተቀየረ ነው።

እስራኤል መጠነ ሰፊ የሆነ ጥቃት ቢከፈትባት በሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ከሚገኙ ሆስፒታሎች ታካሚዎችን ከምድር በታች ወስዶ ማከም ከመቻሉ በተጨማሪ፤ በጦርነት የሚቆስሉ ተጎጂዎችን የመርዳታ አቅም አለው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሃሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *