ፎገራ ÷ ሊሞ ከምከም እና ደራ ወረዳዎች ከጣና ተፋሰስ ዙሪያ ላይ በርብ እና ጉመራ ወንዝ ዝናቡን ተከትሎ ጎርፍ ሊከስትባቸዉ እንደሚችል ታዉቋል።
በክልሉ በተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች ምክንያት የአደጋ ስጋቱን ለመቀነስ በቂ ስራዎች ማከናወን አለመቻሉን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ለኢትዩ ኤፍም ተናግረዋል።
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የደብብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጥላሁን ደጀኔ በዞኑ ባለፍት። ሁለት ቀናት የዝናብ መጠኑ ዝቅ ያለ ቢሆንም በቀጣዩቹ ቀናት በ 21 ቀበሌዎች ጎርፍ ሊያጋጥም እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ዋና አስተዳዳሪዉ በተለይም በፎገራ ወረዳ ከፍተኛ ስጋት እንዳለ ያነሱ ሲሆን በደራ 22 ኪ.ሜ, በሊሙ ከምከም 8 ኪ.ሜ የጎርፍ መቀልበሻ መሰራቱን ገልፀዉ በፎገራ ወረዳ በበጀት እጥረት ምክንያት በተፈለገዉ ልክ መስራት አልቻልም ብለዋል።
የላይኛዉ እና ታችኛዉ የርብ ኘሮጀክት መጠናቀቅ ባለመቻሉም የጎርፍ ስጋቱን እንደሚጨምረዉ ታዉቋል።
በ 9 ቀበሌዎች 56 ሺህ የህብረተሰብ ክፍሎች በጎርፍ አደጋ ስጋት ላይ መሆናቸው በመለየቱ ነዋሪዎቹን ወደ ሌላ ቦታ የማስፈር ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።
የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በኮሚቴ ደረጃ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የዞኑ አስተዳዳሪ አደጋ ከተከሰተ የጀልባ እጥረት ሊያጋጥማቸዉ እንደሚችል ተናገረው።
ዝናቡ ተጠናክሮ ሊቀጥል ስለሚችል ከክልሉም ሆነ ከፊደራል መንግስት ዞኑ ለሚገጥመዉ የጎርፍ አደጋ ግብረ ሀይል በመላክ ትብብር እንዳይለያቸዉ አሳስበዋል።
በየአመቱ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆነዉ ይህ ዞን ዘላቂ የሆነ መፍትሔ እንዲሰራ እና ዉሀ ለአካባቢው ህዝብ ስጋት እንዳይሆን መስራት ይገባል ብለዋል
በቁምነገር አየለ
ነሐሴ 03 ቀን 2016 ዓ.ም
