በፓሪስ ኦሎምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡

በፓሪስ ኦሎምፒክ ድል ያስመዘገቡ እና የተሳተፉ የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የልኡካን ቡድኑ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በዛሬው እለት ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተ-መንግስት ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ለልዑካን ቡድኑ የክብር ሽልማት፣ የማበረታቻ እና የእራት ግብዣ መርኃ-ግብር የሚካሄድ መሆኑንም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ በ33ኛው የፓሪስ ኦሊምፒክ 1 የወርቅ እና 3 የብር በአጠቃላይ 4 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 4ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 07 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *