በተጠናቀቀው የ2016 በጀት አመት በአዲስ አበባ ይፈጸሙ የነበሩ ከባድ ወንጀሎች በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኝነት ሀላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ ከተማዋ ሰላሟ የተረጋገጠ ለማድረግ በተሰራው ስራ በተለያዩ ዘርፎች ውጤት ሊመዘገብ ችሏል።
በአመቱ በከተማዋ በርካታ ሁነቶች እንደመደረጋቸው መጠን ፖሊስ ሰፊ ስራ እና ዝግጅት በማድረግ ሁነቶቹ በሰላም እንዲጠናቀቁ ሀላፊነቱን ሊወጣ መቻሉን ገልጸዋል።
በከተማዋ በተደጋጋሚ ይፈጸም የነበረው የመኪና ስርቆትም በከፍተኛ መጠን መቀነሱን የተናገሩት ኮማንደር ማርቆስ፣ ለዚህም ኮሚሽኑ አሰራሩን በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረጉ የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል።
በመዲናዋ በተለያየ ደረጃ ይፈጸሙ የነበሩ የሞባይል ስርቆት፣ ቅሚያና ንጥቂያ ያሉ የስርቆት አይነቶችም መቀነሳቸውንም ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም
