መጠሪያዬ አልበም 12 ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን አልበሙን ስርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት መፍጀቱን ድምፃዊቷ አስታውቃለች።
ይህ መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ 4 ሙዚቃዎችን ፣ አቡዲ 7 ሙዚቃ እና ሱራፌል የሺጥላ 1 ሙዚቃ በግጥም እና ዜማ መሳተፋቸው ተገልጿል
እንዲሁም በሙዚቃ ቅንብር ታምሩ አማረ ፤አዲስ ፍቃዱ፣ አብርሃም ኪዳኔ፣ ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ሀ/ማሪያም መስራታቸውን ሰምተናል።
አልበሙ ስለፍቅር፣ስለሰላም፣ ስለሀገር ፣ስለተስፋ እና ስለምስጋና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን የዳሰሰ ነው ተብሏል ፡፡
መጠሪያዬ አልበም በሯሷ በድምፃዊቷ የዩትዩብ ቻናል እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
አልበሙ ነሀሴ 17 ይለቀቅ የነበረ ቢሆንም ህፃን ሄቨን ላይ በደረሰው ጥቃት ተከትሎ ብዙ ኪሳራ ቢኖረውም ለነሀሴ 23 መዘዋወሩ ተነግሯል።
መጠሪያዬ የተሰኘውን አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተሰኘ አለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር መስማማታቸው ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ብር አስራ ሰባት ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ይህም ክፍያ በኢትዮጵያ አልበም ክፍያ ታሪክ ከፍተኛ ያደረገዋል ተብሏል፡፡
ዞጃክ ወርልድ ዋይድ መቀመጫውን በአሜሪካ ፍሎሪዳ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ አለማት ማለትም ሜክሲኮ፤ኢንዶኒዢያ ጀማይካ እና ኬንያ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ይህ ካምፓኒ የኢትዮጵያን አልበም ሲገዛ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል ።
ኪነት ኢንተርቴመንት የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ መጠሪያዬ የተሰኘው የመጀመሪያ አልበም ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡
በሐመረ ፍሬዉ
ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም
