በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የበላይነት የሚከናወነው የሀገሪቱ ከፍተኛው የሊግ እርከን ውድድር ቀጣይ ዓመት ውድድር ከመስከረም 10 ጀምሮ እንደሚያከናውን መገለፁ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም በአክሲዮን ማኅበሩ ዋና ፅህፈት ቤት የውድድር ዓመቱ የእጣ ማውጣት መርሐ-ግብር ተከናውኗል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ እና የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ባህሩ ጥላሁን የውድድር ዓመቱን መርሐ-ግብር የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት አውጥተዋል።
– ውድድሩ መስከረም 10 ድሬዳዋ ላይ ይጀምራል ውድድሩ በ19 ክለቦች መካከል ይደረጋል፣አጠቃላይ በዓመቱ 36 የጨዋታ ሳምንታት ይኖራሉ
- አጠቃላይ በዓመቱ 342 ጨዋታዎች ይደረጋሉ ፣በጨዋታ ሳምንታት መካከል አንድ የዕረፍት ቀን ብቻ ይኖራል፣ በአንድ የጨዋታ ሳምንት አንድ አራፊ ቡድን ይኖራል ፣በአንድ የጨዋታ ሳምንት 9 ጨዋታዎች ይደረጋሉ፣ በአንድ የጨዋታ ሳምንት አራት የጨዋታ ቀናት የሚኖሩ ሲሆን በሦስቱ ቀናት ሁለት ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ቀን ሦስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፣የሸገር ደርቢ ጨዋታ በ18ኛ ሳምንት የሚከናወን ይሆናል ። በዚህም መሰርት የ 1ኛ ሳምንት መረሐ -ኃብር
መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀዲያ ሆሳዕና
እትዮ ኤሌክትሪክ ከ ወላይታ ዲቻ
አዳማ ከተማ ከ ሰሒል ሸረ
አርባምንጭ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ
ሲዳማ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ
ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ወልዋሎ ዓ/ዩ ከ ባህር ዳር ከተማ
ወልቂጤ ከተማ ከ መቻል
ኢትዮጵያ መድን የሳምንቱ አራፊ ቡድን ምሆኑ ታውቋል።
በጋዲሳ መገርሳ
ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
