በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ- ግብር እስካሁን 234 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።
በአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀምበር 600 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች እየተካሄደ ይገኛል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ሰላማዊት ካሳ÷ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስካሁን 234 ሚሊየን ችግኝ መተከሉን ገልጸዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም
