በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ በመሬት መንሸራተቱ አደጋ የሟቾች ቁጥር ማሻቀቡ ተሰማምቷል፡፡

የወረዳው ግብርና ቢሮ ሃላፊ ግዛው ዘነበ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደገለጹት ዐርብ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም. አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት በመኖሪያ ቤታቸው ሳሉ በናዳ የተቀበሩ ሰዎችን በመፈለግ በነበረው ሂደት በድጋሚ በተከሰተ አደጋ የሰዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው እስካሁን ከ አስር በላይ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የጠቀሱት አቶ ጋሻው እስካሁን በናዳው ህይወታቸው እንዳለፈ የሚገመቱ ሰዎች አስክሬን ሙሉ በሙሉ አለመገኘቱን ነግረውናል፡፡

በአደጋው ከሞቱት በተጨማሪም በ12 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

የመሬት መንሸራተቱ በአጠቃላይ ከ260 በላይ ሔክታር መሬትን እንደሸፈነ የገለጹት አቶ ግዛው፣ ሌላ አደጋም ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት ከ2 ሺህ 400 በላይ ነዋሪዎች ከአካባቢው እንዲነሱ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

በአደጋው ከ11 በላይ ቤቶች እንደወደሙ እና ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸውንም አቶ ግዛው ጠቁመዋል፡፡

በተያያዘም ከሰብል አኳያ ከ30 ሺ በላይ ሄክታር መሬት ሰብል መወደሙን ገልጸው እንዲሁም ወደ 35 የሚጠጋ በግ እና ፍየል አብሮ እንደወደመም ነግረውናል፡፡

ማህበረሱብ ከአካባቢው ለመልቀቅ ፍቃደኛ ያለመሆን መፍተሄ ያማፈላለግ ሂደቱ ላይ ችግር እንደፈጠረባቸው ጨምረው ነግረውናል፡፡

አሁን ላይ መሬቱ ስላልረጋ ሌላ አደጋ ይከሰታል በሚል ስጋት አስክሬን ፍለጋው ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ተደርጓል ያሉት ሃላፊው ወደ አካባቢው ሰዎች እንዳይሄዱም የፀጥታ ኃይል መሰማራቱንም ነግረውናል።

በለአለም አሰፋ

ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *