በጤፍ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እና በህገወጥ መንገድ ክምችት የሚፈጽሙ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር ይደረጋል ተባለ::
በአዲስ አበባ ከተማ በሸቀጦች ላይ የዋጋ ጭማሪ እና ክምችት አስመልክቶ በተደረገ የቁጥጥር ስራ 1 ሺህ 7 መቶ ነጋዴዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው ተነግሯል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ሰውነት አየለ፣ ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶች እና በኮንስትራክሽን ምርቶች ላይ የሚካሄደው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
በተከናወነው የቁጥጥር ስራ በ460 የንግድ ድርጅቶች ላይ የማሽግ እርምጃ መወሰዱን እንዲሁም በሌሎች ላይ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሊሰጣቸው መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
ነጋዴዎች ለሚሸጡት ምርት የወጋ ዝርዘር መለጠፍ እንደሚኖርባቸውም ተመላክቷል፡፡
ህብረተሰቡ የሚያስታውላቸውን ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በ8585 ላይ ጥቁማ ማቅረብ እንደሚቻልም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በእሌኒ ግዛቸው
ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም
