ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ለልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል የሁለት መቶ ሺሕ ብር ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።
የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር እመቤት መለሰ እና የልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል ተወካይ የሆኑት አቶ ሕሩይ ዓሊ በተገኙበት የገንዘብ ድጋፍ ርክክቡ ተካሂዷል፡፡
የልብ ህሙማን ሕጻናት መርጃ ማዕከል አሁን ላይ ለታካሚዎች አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝበት የልብ አልትራሳውንድ ምርመራ መስጫ ማሽን ከ4 ዓመታት በፊት ከሶስት ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ መግዛቱን ባንኩ አመልክቷል።
እንዲሁም ከ700 በላይ የልብ ሕሙማን ሕጻናት የነጻ የምርመራ አገልግሎት እንዲያገኙ ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አብራርቷል።
አቤል እስጢፋኖስ
ነሐሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም
