በመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)የመስከረም ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነሐሴ ወር ሲሸጥበት በነበረው ዋጋ እንደሚቀጥል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ስለሆነም የነዳጅ ማደያዎች ያልተገባ ምርት ሳያከማቹና የዋጋ ጭማሪ ሳያደርጉ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *