ሚኒስትሮች በተሸለሙበት መድረክ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሽልማት ተበረከተለት።
በውሀና ኤነርጂ ጉዳዮች ኢትዮ ኤፍ ኤም በሰራቸው ዘገባዎች ነው ተሸላሚ የሆነው።
የውሀና ኤነርጂ ሚኒስትር ባዘጋጀው የምስጋና ፕሮግራም ኢትዮ ኤፍ ኤም በውሀና ኤነርጂ ጉዳይ በሰራቸው የዘገባ ሽፋን ተሸላሚ ተደርጓል።
ሽልማቱን ያበረከቱት የውሀና ኤነርጂ ሚኒስትር ዶር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ናቸው።
ሚኒስትር መስራቤቱ የቀድሞ ተቋሙን የመሩ ሚኒስትሮቹን ባመሰገነበት መድረክ የሚዲያ ተቋማት ስለሰሩት ዘገባ በተመሳሳይ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
እውቅና ሽልማት ከተበረከተላቸው የቀድሞ ሚኒስትሮች መካከል ራስ ልዑል መንገሻ ስዩም እንዲሁም ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ስጥታ ከተበረከተላቸው መካከል ሲሆኑ አቶ ሞቱማ መቃሳ ፣አቶ አለማየሁ ተገኑ እንዲሁም አምባሳደር ሽፈራሁ ጃርሶ የምስጋና ሽልማት ከተበረከተላቸው የቀድሞ አመራሮች መካከል ይገኙበታል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም
