በዛሬው እለት ጳጉሜ 4 ቀን 2016 አመት እየተከበረ የሚገኝው የህብር ቀን ወረዳው በተለያዩ ሁነቶች እያከበረ ይገኛል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት ስራ አስፈጻሚ አቶ አዱኛ ዘበነ ቀኑን በማስመልከት በወረዳው ለሚገኙ ለ2ሺህ አምስት ዜጎች የበአል ማሳለፍያ የሚሆን የአይነት ድጋፍ እንደተደረገላቸው ተናግረዋል።
ለዜጎቹ የተደረገላቸው እገዛ ለእያንዳንዳቸው 3ሺህ 500 ብር እንደሆነ ተናግረው የኢትዮጵያዊያን የመረዳዳት ባህላችንን ለማሳየት ነው ይህ የተደረገው ብለዋል፡፡
እንዲሁም የአቃቂ ቃሊቲ ወረዳ ሁለት የብልጽግና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀይሌ ደበሌ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የህብር ቀን እያከበረች በምትገኝበት ቀን አቅመ ደካማ ለሆኑ ዜጎች ወረዳው አመስት ሚሊዮን ብር በማውጣት ቤታቸው ማደሱን ነው ገልጸዋል።
ይህንን እውን እንዲሆን ትብብር ያደረጉ ባለሀብቶች ቅን ልብ ያላቸው የወረዳው ነዋሪዎች አስተዋጾቸው የላቀ ነበር ብለዋል።
ኢትዮጵያ የነገ ትልሞቿን ለማሳካት ኢትዮጵያዊያን በህብረት መቆም ይገባናል ያሉት ሀላፊው አመቱን በመረዳዳት ልናከብረው ይገባል ብለዋል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም
