“አሽከርካሪዎች በዓል ሳትሉ በሁሉም ጊዜና ሁኔታ ህዝብን ስለምታገለግሉ ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል” — ዶ/ር አለሙ ስሜ

ዶ/ር አለሙ ስሜ በላምበረትና አዲስ ከተማ(አውቶቢስ ተራ) የህዝብ ትራንስፖርት ተርሚናሎች ተገኝተው አሽከርካሪዎች ምስጋናና የመልካም በዓል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፋት መልዕክት አሽከርካሪዎች በዓል ሳትሉ በሁሉም ጊዜና ሁኔታ ህዝብን ስለምታገለግሉ ትልቅ ክብርና ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል።

ዛሬ ከንጋቱ 10:00 ጀምሮ በበዓል ዋዜማ በሰራ ላይ የሚገኙ አሽከርካሪዎችና በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማክበር የሚሄዱ መንገደኞች ሚኒስትሩ የበዓል የአበባየሆሽ ዝማሬ ከሚያቀርቡ ታዳጊዎች ጋር ነው በተርሚናሎቹ የተገኙት።

በዓልን በስራ ላይ እያሳለፋ ያሉት አሽከርካሪዎች ከሚኒስትሩ ስለአገልግሎታቸው ምስጋናና የመልካም በዓል ካርድ ስጦታም ተበርክቶላቸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጳጉሜ 05 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *