ሩሲያ በስለላ ወንጀል የጠረጠረቻቸውን ስድስት የብሪታኒያ ዲፕሎማቶችን ዕውቅና መሰረዟን አስታውቃለች፡፡

የሩሲያ የፀጥታ እና ደህንነት አገልግሎት ዲፕሎማቶቹ የሩሲያን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ዲፕሎማቶቹ በምስራቅ አውሮፓ እና በመካከለኛው እስያ ያለውን የፖለቲካ እና ወታደራዊ ሁኔታ እንዲያስተባብሩ እንዲሁም እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሩሲያ እንድትሸነፍ ስትራቴጂካዊ እቅድ እንዲያወጡ ሃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር ብሏል፡፡

በዚህም የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስድስቱ የብሪታኒያ ዲፕሎማቶች እውቅና በመሰረዝ ከሀገሪቱ እንዲወጡ መወሰኑ ተገልጿል።

ብሪታኒያ በጉዳዩ ላይ ያለችው ነገር አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

መስከረም 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *