በዚህም የአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አስተዳዳሪ በአንድ ወገን ለአራት ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳው ማንቺስተር ሲቲ በሌላ ወገን ሆነው ከሥነ ምግባር ኮሚሽን ዳኞች ፊት ይቆማሉ።
በክሱ ሂደት ማንችስተር ሲቲ የፕሪሚየር ሊጉን የፋይናንስ ህግጋት ጥሷል በሚል የቀረቡበት 115 ክሶች መታየት ይጀምራሉ።
የክፍለ ዘመኑ ታላቅ የስፖርት ክስ በሚል የተጠራው ይህ የፍርድ ቤት ጉዳይ ለ10 ሳምንታት እንደሚቆይ የሚጠበቅ ሲሆን ብያኔው በፈረንጆች 2025 ይሰጣል የሚል ግምት አለ።
በአንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግና በአውሮፓ ኃያል የሆነው ሲቲ ለበርካታ ዓመታት የፋይናንስ ህጉን ሲጥስ እና ‘ሲያጭበረብር’ ነበር የሚል ክስ ይቀርብበታል።
ማንችስትር ሲቲ በ14 የውድድር ዘመኖች ፈፀሞታል ተብሎ ከቀረበበት 115 ክስ መካከል ትክክለኛ የፋይናንስ ማስረጃ አላቀረበም የሚል ተካቶበታል።
ማንችስተር ሲቲ በክሶቹ ጥፋተኛ ሆኖ የሚገኝ ከሆነ ስሙ በዓለም ትልቅ ከሆነው የስፖርት ክስ ታሪክ ጋር በማጭበርበር ቅሌት ተያዘይዞ ይነሳል።
በብያኔው ደግሞ ወደ ታችኛው ሊግ ሊወርድ በሚያስችል ደረጃ ነጥቡ ይቀነሳል አሊያም ከፕሪሚየር ሊጉ ሊባረር ይችላል።
የማንችስትር ሲቲ 115 ክሶች ምንድን ናቸው?
ከ2009 – 10 እስከ 2017 -18 ባሉት የውድድር ዘመኖች ትክክለኛ የፋይናንስ መረጃውን አላቀረበም በሚል 54 ክሶች
ከ2009 – 10 እስከ 2017 -18 ባሉት የውድድር ዘመኖች የተጫዋቾችን እና አሰልጣኙን ትክክለኛ የደሞዝ መጠን አለቀረበም የሚል 14 ክሶች
ከ2013 – 14 እስከ 2017 -18 ባሉት የወድድር ዘመኖች የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የፋይናንስ ጨዋነትን (Financial Fair Play) በመጣስ 5 ክሶች
ከ2015 – 16 እስከ 2017 -18 ባሉት የወድድር ዘመኖች የፕሬሜሪ ሊጉን የፕሮፌሽናልነት ህግ በመጣስ 7 ክሶች
35 ክሶች በአውሮፓውያኑ ከ2018 እስከ 2023 ለፕሪሚየር ሊጉ ጋር ባለመተባበር ቀርበውበታል።
ዋና አሰልጣኙን ጉዋርዲዮላን ጨምሮ የሲቲ አመራሮች ሁልጌዜም ‘እጃችን ንጹህ ነው’ በሚል ስሜት በከፍተኛ በራስ መተማመን ይናገራሉ።
በርካቶች የዚህን ችሎት ብያኔ በጉጉት እየጠበቁ በርካታ መላምቶችን ሊያስቀምጡ ይችላሉ። ትክክለኛው ውሳኔው የሚገኘው ግን ከገለልተኛው የሥነ ምግባር ኮሚሽን ይሆናል።
ማንችስተር ሲቲ የአለማችን ምርጥ ጠበቃ አንዱ ለሆነው ሎርድ ፓኒክ በሰአት £5,000 ይከፍላል እናም የክሱ ጉዳይ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያመራ ከሆነ በሰአት £80,000 ፓውንድ ይከፍላል::
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም
