36 ክለቦች እንደ አዲስ በተዋቀረው ውድድር ላይ ይሳተፋሉ። ቀደም ሲል ለባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ ይፋለሙ የነበሩት 32 ቡድኖች ብቻ ነበሩ።
ፍጻሜውን ሙኒክ ላይ የሚያደርግ የሆናል።
የሻምፒዮንስ ሊግ አሸናፊ ማን ይሆናል?
1 ሪያል ማድሪድ ።
ምክንያት ያደግሞ የክሊያን ምባፔ ቡድኑን መቀላቀልን ነው ። ማድሪድ ዋንጫውን ደጋግሞ ማንሳቱ ውድድሩን አሰልቺ አድርጎታል። ዘንድሮም ተለየ ነገር አይኖርም
የስፔኑ ቡድን ለዚህ የሚሆን ልምድ፣ ታሪክ፣ ገንዘብ፣ ጊዜ፣ ጥንካሬ እና ችሎታ አለው
ከማድሪድ በመቀጠል ደግሞ ማንቸስተር ሲቲ እና ባየር ሙኒክ ዕድል አላቸው ።
ማድሪድ የኮከብ ተጫዋቾች መሰባሰቢያ መሆኑን በድጋሚ ቢያሳይም፤ ዘንድሮ ግን ዋንጫው የማንቸስተር ሲቲ ሊሆና ያችላል።
ኤርሊንግ ሃላንድ ክረምቱን በማረፉ እና ቡድኑ ከያዘው የፈጠራ ክህሎት እና ልምድ አንጻር ዋንጫውን ሊያነሳ ያችላል።
አዳዲስ አሠልጣኝ የቀጠሩት ሙኒክ እና ባርሴሎና ጊዜ ይፈልጋሉ። አርሰናል ደግሞ ትኩረቱ የሊጉ ዋንጫ ላይ ነው። በዚህ ጊዜ ውስጥ ማንቸስተር ሲቲ በልምድ እየዳበረ በተለያዩ መንገዶች ማሸነፍን እየለመደ ነው ።
የውድድሩ አስደናቂ ቡድን ሊሆኑ የሚቺሉ ክለቦቸ
1 ሊቨርፑል
የርገን ክሎፕ ከቡድኑ ጋር ባይሆኑም ቡድኑ ወደ ጥሎ ማለፈ ከተሸጋገረ ለተፎካካሪዎች ከባድ ይሆናል።
በአሠልጣኝ አርን ስሎት የሚመራው ቡድን አሁንም ድንቅ ተጫዋቾችን ይዟል።
አሠልጣኙ በአውሮፓ መድረክ ያለውን ታክቲካዊ ፉክክር ለመጋፈጥ ዝግጁ ናቸው።
2 ባየር ሊቨርኩሰን
አዲሱ የሻምፒዮንስ ሊግ መዋቅር ከታላላቅ ቡድኖች ውጪ ላሉ ቡድኖች ዕድል የሚሰጥ ነው።
ሊቨርኩሰን ደግሞ የውድድር ዓመቱ አስገራሚ ቡድን ሊሆን ይችላል።
ዣቪ አሎንሶ እና ቡድናቸው ባለፈው የውድድር ዓመት የሊጉን ዋንጫ ያነሱበትን ጉዞ በትልቁ መድረክ ለማሳየት ይሞክራሉ።
3 ኢንተር ሚላን
ስኩዴቶው የጁቬንቱስን የበላይነት ከማስቆም በተጨማሪ በአውሮፓ መድረክ በተደጋጋሚ እየተሳተፉ ነው።
እንደ ላውታሮ ማርቲኔዝ ያሉ ኮከቦቻቸውን ከማቆየታቸውም በላይ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርመዋል።
4 አትሌቲኮ ማድሪድ
ቡድኑ እንድ ዩሊያን አልቫሬዝ እና ኮኖር ካላገር ያሉ ተጫዋቾችን በማስፈረም ተጠናክሯል።
ቡድኑ በአሰልጣኝ ዲዬጎ ሲሞኔ ስር ለሁለት ጊዜ ለፍጻሜ መድረሱም መዘንጋት የለበትም ።
የዘንድሮ ተጠበቂውቹ ተጫዋቾች
1 ኪልያን ኤምባፔ
2 ኤርሊንግ ሃላንድ
3 ሀሪ ኬን
4 ቪኒ ዡኒየር
5 ላሚን ያማል
6 ጁድ ቤሊንግሀም
7 ቡካዮ ሳካ
8 ራፋኤል ሊያኦ
9 ቪክተር ጋይኮረስ
10 ፋቢያን ሩይዝ
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች !
01:45 | ጁቬንቱስ ከ ፒኤስ ቪ
01:45 | ያንግ ቦይስ ከ አስቶን ቪላ
04:00 | ኤሲ ሚላን ከ ሊቨርፑል
04:00 | ባየር ሙኒክ ከ ሳልዝበርግ
04:00 | ሪያል ማድሪድ ከ ስቱትጋርት
04:00 | ስፖርቲንግ ሊዝበን ከ ሊል
በጋዲሳ መገርሳ
መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም
