በሊባኖስ በኮምኒኬሽን መሳሪያዎች እየተፈፀመ ስላለዉ ጥቃት የአዉሮፓ ህብረት ስጋቱን ገለፀ።

የአዉሮፓ ህብረት የዉጪ ጉዳይ ፖሊሲ ሀላፊዉ ጆሴኘ ፔሮል በሊባኖስ በፔጃር የሬድዩ መገናኛ ላይ የሚያነጣጥሩ ጥቃቶችን አዉግዘዋል።

በሁለት ቀናት ዉሰጥ በሊባኖስ በተደረሰዉ ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸዉ ታዉቋል። 3500 ያህሉ ደግሞ መቁሰላቸዉ በሀገሪቱ ጤና ሚኒሰትር ተገልጿል።

ይህ ጥቅም ላይ የዋለዉ ተቀባይነት የሌለዉ የጥቃት ዘዴ አስከፊ መዘዝ ያለዉ በመሆኑ አስቸኳይ ቅስቀሳ ያስፈልገዋል ብለዋል ቦሬል

ጆሴፍ ቦሬል የአዉሮፓ ህብረት በቀጠና ያለዉን ስጋት ለማስወገድ የተቻለዉን ያደርጋል ብለዋል አያይዘውም ጦርነት ለማስወገድ ለባለ ድርሻ አካላት ጥሪ አቅርበዋል።

በትናንቱ ጥቃት ሂዝቦላህ እስራኤልን ተጠያቂ በማድረግ የደረሰውን አስከፊ ፍንዳታ ተከትሎ አፀፋውን ለመመለስ ቃል ገብቷል።

በእስራኤል እና በሂዝቦላ መካከል ያለው ግጭት ወደ ሙሉ ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል የሚል ስጋት እንዳደረባቸው የአዉሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲኘሎማት ጆሴፕ ፔሮል ገልፀዋል።

ዘገባዉ የፔሬስ ቲቪ ነዉ።

ቁምነገር አየለ

መስከረም 9 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *