ጋንግሪን(gangrene)

ጋንግሪን አደገኛ እና ገዳይ የሆነ የጤና ችግር እንደሆነ  ይነገራል ፡፡
ስር የሰደደ የጤና እክል ያለባቸው እና የበሽታ መከላከል አቅማቸው የተዳከመ ሰዎች ለዚህ ሕመም ተጋላጭ መሆናቸው ይነሳል፡፡

የጋንግሪን ህመም በተለምዶ በእግር ላይ የሚስተዋል ቢሆንም በየትኛዉም የሰዉነታችን ክፍል ላይ የሚከሰት ህመም ነዉ፡፡

በጉዳዩ ላይ ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታልና በላንሴት አጠቃላይ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ጥገና ፣ቅየራና የከፍተኛ ስብራቶች ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶ/ር ገለታው ተሰማ ናቸዉ።

ጋንግሪን ማለት ምን ማለት ነዉ?

ከሙሉ አካላችን ተለይቶ የተወሰነ የሰዉነት ክፍላችን እየሞተ ወይም በድን እየሆነ መምጣት ነው ይላሉ፡፡

ይህም በዛ አካባቢ ያሉት የሰዉነት ክፍላችን በቂ የሆነ ደም ፣ ኦክስጅን  እና ምግብ ባለማግኘቱ የሚፈጠር እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው?

–  የስኳር ታማሚ መሆን
–  ኢንፌክሽን
–  በአደጋ ምክንያት የደም ስር መቆረጥ ተጠቃሽ መሆናቸውንም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡

የስኳር ህመምተኞችም ማድረግ ካለባቸው ጥንቃቄዎች መካከል የሚያጠብቃቸውን ጫማ ከመልበስ መቆጠብ እንደሆነ  አንስተዋል፡፡

ምልክቶቹ ምንድን ናቸው?

–  እዛ አካባቢ ላይ መጥቆር እና
–  መድረቅ ዋናዎቹ መሆናቸዉንም ዶክተር ገለታዉ ነግረዉናል፡፡

ህክምናዎቹ ምንድን ናቸው?

የሚሰጡት ህክምናዎች እንደየ ምክንያቱ እንደሚለያይም ባለሙያዉ ይናገራሉ፡፡
–  ለአንዳንድ ሰዎች የደም ስር ህክምና የሚሰጥ ሲሆን፤
–  ኢንፌክሽኑን ማከም
–  ከፍ ካለ ደግሞ የተጎዳውን አካል ማስወገድ ከህክምናዎቹ መካከል መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የስኳር ህመምተኞች ተገቢውን የህክምና ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው እና በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጧቸውን የጥንቃቄ  መልዕክቶች መከተል እንዳለባቸዉ ዶ/ር ገለታው ተናግረዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *