ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ በሐዋሳ ከተማ የጨፌ ቆንቦዬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የማስፋፈያ ፕሮጀከት ዛሬ ኅዳር 5 ቀን 2017 ዓ.ም አጠናቅቆ ለማሕበረሠቡ አስረክቧል።
የቢጂአይ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሚስተር ኸርቬ ሚልሃድ፤የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የተሰራው በስድስት ወራት ውስጥ ነው ብለዋል።
ይህ የትምህርት ቤት የማስፋፊያ ፕሮጄክት በአንድ ፈረቃ ከ 525 በላይ አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ እንዲያስተምር ይረዳል ብለዋል።
ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ብር በመመደብ በ2024 በአከባቢ ልማት፣ጤና እና የትምህርት ቤት ግንባታ ላይ ትኩረት በማድረግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ተብሏል ።
የሃዋ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ በየነ በራሳ በበኩላቸው፤ዛሬ “በሐዋሳ ከተማ የተመረቀው ይህ ትምህርት ቤት የመጪውን ትውልድ ለመቅረፅ፣ የት/ቤቶችን አቅም ከማሳደግ አንፃር ሚናው የላቀነው ብለዋል።
በተጨማሪም በቀጣይ ትምህርት ቤቱን ሌሎች አስፈላጊ ለመማር ማስተማር የሚረዱ መሰረተ ልማቶቹን ለሟሟላት ይሰራል ብለዋል።
ቢጂአይ የኮምቦልቻና የዘቢዳር ት/ቤቶችን ግንባታቸው የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ለማህበረሰቡ የሚያስከረከብ ይሆናል ተብሏል ።
ኩባንያው በማህበረሰባዊ ኃላፊነት ረገድ አዎንታዊ ለውጥ የማረጋገጥ ተልዕኮውን በማስቀጠል መሠል የመሠረተ ልማት ኢንቨስትመንቶችን በተለያዩ የሃገራችን ከተሞች ላይ የሚቀጥል ይሆናል መባሉን ሰምተናል፡፡
ልኡል ወልዴ
ህዳር 05 ቀን 2017 ዓ.ም
