በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት “የሰው ህይወት ቀጥፏል” መባሉን መንግስት እንዲያጣራ ኢዜማ ጠየቀ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአዲስ አበባ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት “የንፁሀን ዜጎች ህይወት መቀጠፉ እየተሰማ ነው” መሆኑን አሳውቋል፡፡

ፖርቲው ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት የሚገባ ታጣቂ ኃይል ሁሉ ትጥቁን ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።

በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡

“ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም” ሲልም አሳስቧል::

ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትናንት ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በመጓዝ ላይ የነበሩ “የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂ ቡድን አባላት” በአዲስ አበባ በተለያዩ አከባቢዎች ላሰሙት ተኩስ የ አዲስ_አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ይቅርታ መጠየቁ የሚታወስ ነው፡፡

ኀዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *