አዲሱ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ቃለ መሀላ ፈጸሙ፡፡

አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ የሶማሊላንድ ፕሬዝደንት ሆነው ዛሬ ሐሙስ ቃለ መሀላ ፈጸሙ።

ኢሮ በሚል ቅጽል ስማቸው የሚታወቁት የተቃዋሚው ዋዳኒ ፓርቲ መሪ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ 6ኛ ፕሬዝደንት ሆነዋል።

የ69 ዓመቱ አብዲራሕማን ሞሐመድ አብዱላሒ ከዚህ ቀደም የሶማሌላንድ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የነበሩ ናቸው።

ሶማሊላንድ በ እ.ኤ.አ. 1991 ዓ.ም. ነው በተናጠል በወሰደችው ውሳኔ ከሶማሊያ ተለይታ እራስ ገዝነቷን ያወጀችው። እስካሁን ዓለም አቀፍ እውቅና አላገኘችም።

ሆኖም ምርጫውን ለመታዘብ በመላው ሶማሊላንድ ግዛት 28 ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰማራታቸውን አሶሲየትድ ፕረስ ዘግቧል።

ታህሣሥ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *