በየጊዜዉ የሚደረግ የስራ አመራሮች ለዉጥ  ለስራዬ እንቅፋት ሆኗል” ሲል የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ገለፀ።

በጋምቤላ ክልል የሚደረጉ ጊዜን የማይጠብቁ  የአመራር ለዉጦች እንዲሁም  ዝዉዉሮች ለተቋሙ የሚቀርቡ አቤቱታዎች መፍትሔ እንዳያገኙ እክል እንደሆነበት  ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የጋምቤላ ቅርንጫፍ ለኢትዩ ኤፍአኤም እንደገለፀዉ በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ስር ያሉ መዝገቦች እየታዩ ባለበት ሂደት በየተቋማቱ ያሉ የግለሰቦች  መለዋወጥ የዉሳኔ   መጓተት መፍጠሩን አሰታዉቋል።

በኢትዩጵያ ህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም ጋምቤላ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ ግርማ መኩሪያ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ “ጉዳዩን የሚይዘዉ አሰፈፃሚ አካል በተለዋወጠ ቁጥር የአቤቱታ መዝገቦች  እንደ አዲስ የሚታዩ እንጂ ካቆሙበት የሚቀጥሉ አይሆኖም ብለዋል።

እንደ አዲስ እየታዩ ባሉ መዝገቦችም አዲሱ አመራር  መረዳት እንዲኖረዉ  ለማስቻል ባለ ሂደት የአቤቱታዉ ዉሳኔ መዘግየት እንዲታይበት አድርጓል ተብሏል።

በዚህም የአስፈፃሚ አካላት ይህንን ግንዛቤ ወስዶ በሀላፊነት የመስራት ዉስንነት መመልከታቸዉን  የክልሉ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተወካይ አቶ ግርማ መኩሪያ ገልፀዋል።

በጋምቤላ ክልል ተቋሙ በዘንድሮዉ በጀት አመት አጋማሽ 75 አቤቱታዎችን ለመቀበል አቅዶ 36 አቤቱታዎች ብቻ መቅረባቸዉን ለማወቅ ተችሏል።

ከነዚህ አቤቱታዎች ዉስጥ ከመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ የታዩ መዝገቦች በቁጥር ከፍ ያለ መሆኑን ሰምተናል።

በጋምቤላ ክልል የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም እየሰራቸዉ ባሉ ስራዎች የክልሉን ህዝብ ተደራሽ ሆኖ ሀላፊነቱን ለመወጣት ከክልሉ መስተዳድር ጋር እየተወያየ ይገኛልም ተብሏል።

ቁምነገር አየለ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *