የተቋዋሚዎች የጋራ ምክር ቤት ለመመስረት ተገደናል ሲል የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ገለፀ።

የጋራ ምክር ቤቱ  በበኩሉ የፖለቲካ የጋራ ምክር ቤቱ በህጋዊ እና የቃል ኪዳን ሰነድን ሂደት በመከተል ጉባኤ አካሂዶ ስራ ላይ ይገኛል ብሏል።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)   የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ በስራ ላይ ይገኛል ብሎ እንደማያምን አስታውቋል።

የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት መጋቢ ብሉይ  አብርሀም ሀይማኖት  “አሁን ላይ የጋራ ምክር ቤቱ ፈርሷል ብለለን እናምናለን” ያሉ ሲሆን እንደ መፍትሄም የተቋዋሚዎች የጋራ ምክር ቤት ለማቋቋም ማቃዳቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በምክር ቤቱ የተለያዩ የሕግ ጥሰቶች ነበሩ የሚሉት መጋቢ ብሉይ አብርሀም ሀይማኖት ፤ምክር ቤቱ አላግባብ ስልጣን ላይ በመቆየትና የምርጫ ጊዜውን በማራዘም  አሁን ያለበትን ቁመና ይዟል ብለዋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በምንፈልገው መንገድ ባለመሄዱና ጉዳዩንም ወደ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በመውሰድ ምክር ቤቱን እንዲያድነው ጥረት ቢደረግም መፍትሄ ሳይሰጥ ጠቅላላ ጉባኤው መካሄዱ እና አጀንዳ መመረጡም ተገቢ አይደለም አግባብነትም የለውም ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም  የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱን በጉዳዩ ላይ የጠየቀ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ የፓርቲዎችን ክስ አጣጥሏል።

የምክር ቤቱ አዲሱ ተመራጭ ሊቀመንበር አቶ ሰለሞን አየለ  እንዳሉት፤ የምክር ቤቱን ህጋዊ እውቅና በማመን ችግሮችን በምክክር መፍታት ይገባል ብለዋል።

ምክር ቤቱ በተቋቋመበት የቃል ኪዳን ሰነድ አማካኝነት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል የሚሉት አቶ ሰለሞን፤ በዚህም የምክር ቤቱ አንዱ ስራ የሆነውን የጋራ አጀንዳ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ አቅርበናል ብለዋል።

ለአለም አሰፋ

ታኀሣሥ 7 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *