አጎዋ የሚራዘም ከሆነ ኢትዮጵያ ፖለቲካዋን መቃኘት ያስፈልጋታል ተባለ

አጎዋ የሚራዘም ከሆነ ኢትዮጵያ ወደ ገበያው ለመመለስ ፖለቲካዋን መቃኘት ያስፈልጋታል ሲሉ የኢንቨስትመንትና የቢዚነስ አማካሪ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋዬ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸው ቆይታ ነግረውናል።

አማካሪው ኢትዮጵያ ከአጎዋ እንድትወጣ የተደረገው ከንግድ ጋር በተገናኘ ሳይሆ በፖለቲካ አማካኝነት ነው ብለውናል።

ይሁን እና አግዋ እንደ አውሮፓውያኑ በግንቦት 18 በ2000 ዓ.ም በአሜሪካ ኮንግረንስ የጸደቀ ሲሆን በ2025 ክለሳ እንደሚደረግበት በህጉ ሰፍሯል ።

አቶ ይርጋ ታዲያ ኢትዮጵያ ገበያው የሚራዘም ከሆነ  ከአዲሱ የአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ጋር አበክራ መስራት እንደሚገባትና አለም ኢትዮጵያን የሚመለከትበት መነፅር እንዲቀየር መስራት እንደሚገባ ተነግሯል፡፡

የአፍሪካ ዕድገት እና ዕድል ድንጋጌ (አግዋ) በአሜሪካ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉና ከሰሃራ በታች ለሚገኙ አገራት ምርቶቻቸውን ከቀረጥ ነጻ ለአሜሪካ ገበያ እንዲያቀርቡ የሚያስችል ዕድል ወይም ችሮታ ነው።

ኢትዮጵያ በገበያው በርካታ ጠቀሜታ አግኝታ ነበር የተባለ ሲሆን በዛውም ልክ ከገበያው በመታገዷ ከፍተኛ ኪሳራ ገጥሟት ነበረም ብለውናል።

አማካሪው በመደምደሚያ ሃሳባቸው እንዲህ ያሉ እድሎች ሲገኙ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ለጥቃቅንና አነስተኛ ድርጅቶች ጠቃሚ ነው ያሉ ሲሆን በየትኛውም ቦታ፣ጊዜና ሁኔታ ከስጋት ለመዳን ግን በአለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል በምርትና አገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ የፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር የአገዋ ዕድል ተጠቃሚ የነበረችውን ኢትዮጵያን ማገዱ  አይዘነጋም፡፡

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሥ 9  ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *