ኢትዮጲያ ክሪፕቶ ከረንሲን መጠቀም የሚያስችላትን ህግ ልታወጣ ትችላለች ተባለ።

ክሪፕቶ ከረንሲ በሀገር ውስጥ ለመገበያያ እንዲውል ተጠይቋል።

ይህንን በሚመለከት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ኢትዮጵያ ክሪፕቶ ከረንሲን ለመገበያያነት እንድትጠቀም የሚያስችል መመሪያ ልታወጣ እንደምትችል ጠቁመዋል።

የሀሽባል ማይኒንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የቢትኮይን ባለሞያ አቶ ቃል ካሳ የክሪፕቶ ከረንሲ በኢትዮጵያ በህግ ማዕቀፍ ቢፈቀድ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ባለሞያው ከአኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ አሁን ላይ ቢትኮይን እና መሰል የዲጂታል መገበያያዎች ፍቃድ ባያገኝም የቢትኮይን ማይነሮች ግን በሀገር ውስጥ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

በዚህ አመትም 20 የሚጠጉ ቢትኮይን ማይነሮች  55 ሚሊዮን  ብር ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማስገባት መቻላቸውን አቶ ቃል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክም በብሄራዊ ባንክ ገዢው በኩል በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳስታወቀው የክሪፕቶ ከረንሲን  እና የዲጂታል ገንዘብን በኢትዮጵያ መጠቀም የሚያስችል መመሪያ ወደፊት ሊያወጣ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ብሔራዊ ባንክ መመሪያውን የሚያወጣው በማዕከላዊ ባንኪንግ፣ በገንዘብ ፖሊሲ እና በገንዘብ አስተዳደር  ያሉ ዓለም አቀፍ  ለውጦችን እያየ መሆኑንን ገዢው አቶ ማሞ  ተናግረዋል። 

ለአለም አሰፋ

ታኀሣሥ 9  ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *