“ማህበረሰቡ ለተደራረበ የግብር ጫና እየተጋለጠ ነው” የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የንበረት ታክስ ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በውይይቱ ላይ ሃሳበቸውን የገለጹት የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ ( ዶ/ር) ከዚህ ቀደም የኤክሳይዝ ታክስ አሻሽለናል ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስም እንደዛው አሁን ደግሞ የንበረት ታክስ ይጠበቃል ይህ ደግም ህዝቡን ለተደራረበ የግብር ወጪ መዳረግ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በእነዚህ ተደራራቢ በሆኑ የታክስ ማሻሻያዎች በስፋት የሚጎዳው መካከለኛውን እና ዝቅተኛውን የህበረተሰብ ክፍል ነው ብለዋል፡፡

ነጋዴው ማህበረሰብ ቢያንስ መቋቋም ይችላል ሲሉም ተናግረዋል፡፡

“በዚህም ማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ ችግር እና መማረር እንዳይፈጥር ስጋት አለን” ሲሉም የምክር ቤቱ አባል በውይይቱ ላይ ሃሳባቸውን ግልጸዋል፡፡

“የንብረት አዋጁ ግብሩ የሚጣለው የተሻለ ገቢ ባለው ላይ ነው የሚጣለው ይላል ኢትዮጵያ ውስጥ የተሻለ ገቢስ ስንት ነው” ሲሉ የምክር ቤቱ አባል አንስተዋል፡፡

ውይይቱ እንደቀጠለ ሲሆን አዋጁ ከመጽደቁ በፊት ግልጽ በሆነ መልኩ ህዘቡን ማወያየትም ይጠበቃል ሲሉም የምክርቤቱ አባላት ሃሳባቸውን እየሰጡ ይገኛል፡፡

ለዓለም አሰፋ

ታኀሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *