በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ የሚተላለፉ እገዳዎች የሲቪክ ምህዳሩን በማጥበብ በማህበር የመደራጀት መብት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳይፈጥሩ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡
ኢሰመኮ፤ተቋሟቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸው አሳሳቢ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ነዉ ያለዉ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን 3 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ላይ እገዳ ማስተላለፉን ተከትሎ በቀረቡለት አቤቱታዎች እና በደረሰው መረጃ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶቹ “ከፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ መሥራት ሲገባው ከዓላማው ውጭ በመንቀሳቀስ የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ ተግባራት ላይ መሰማራቱ” የሚል የእገዳ ደብዳቤ እንደደረሳቸዉ ለማወቅ ችያለሁ ብሏል፡፡
ኢሰመኮ ጉዳዩን በመከታተል ላይ እያለ ተጨማሪ 2 በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ የሚሠሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተመሳሳይ ይዘት ባለው እና ተቋሟቱ የፈጸሟቸውን ከባድ የሕግ ጥሰቶች በዝርዝር ባላስቀመጠ ደብዳቤ መታገዳቸው አሳሳቢ ነዉ ሲል ኢሰመኮ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ታኅሣሥ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በጻፈዉ ደብዳቤ በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሠሩትን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እና የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልንም ማገዱን ገልጿል።
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
