አመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ለሰባተኛ ጊዜ ከዛሬ ታህሳስ 18 ጀምሮ እስከ ታህሳስ 20 ቀን 2017 በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ለጎብኚዎች ክፍት ተደርጎል።
ኢትዮጵያ በቤት ልማት ዘርፍ እያሳደገች ያለችውን እድገት ተከትሎ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት እንደተጀመረ ተገልጿል ፡፡
ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤከስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከቤት ባለቤቶች፣ ከገዥዎች፣ ከሻጮች፣ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ቀዳሚ ኤግዚቢሽን ነዉ ተብሏል ፡፡
በዘንድሮው ኤግዚብሽን ሻጩን እና ገዢውን ከማገናኘት ባለፈ የፖሊሲ አውጪዎች እና ውሳኔ ሰጪዎች ከአልሚዎች ጋር ማቀራረብ ያለመ ተነግሮል ፡፡
በቤት ልማት እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ ያሏትን እድሎች ለመምከር በግሉ እና በመንግስት ዘርፍ ድልድይ ለመሆን የኢትዮጵያ ከተማና ልማት ሚኒስቴር፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን እንዲሁም የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ተወካዮች ዉይይት አድርገዋል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
