የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን ለማግኘት መረጃዎች እንደሚጠየቁም ተገልጿል፡፡
ትምህርት ቤት ለመመዝገብ የልደት ካርድ እና የክትባት ወረቀት ይጠየቃሉ ነዉ የተባለዉ፡፡
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር መከላከል እና መቆጣጠር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ፤ ልጆቹ በመደበኛዉ ስርዓት ዉስጥ የነበሩ ባለመሆናቸዉ የሚጠየቁትን ማስረጃዎች ማቅረብ አይችሉም ብለዋል፡፡
የልደት ካርድ እና የክትባት ወረቀቶች ቢኖሯቸዉም አብዛኛዎቹ ይዘዉ ስለማይመጡ አገልግሎቱን ለማግኘት እየተቸገሩ መሆናቸዉን አንስተዋል፡፡
የመንግስት ብቻ ሳይሆን የግል ትምህርት ቤቶችም በአስገዳጅ ሁኔታ መረጃዎችን ይጠይቃሉ ያሉት አቶ ደረጄ፤ ማህበረሰቡንም ሆነ የሚመለከታቸዉ አካላትን ማስገንዘብ ያስፈልጋል፡፡
መደበኛ ባልሆነ መንገድ በአረብ አገራት የነበሩ ወደ 8 ሺህ ህጻናትን ተቀብለናል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚዉ፤ ልጆቹ በአብዛኛዎቹ አባት የሌላቸዉ መሆናቸዉንም አንስተዋል፡፡
ሊዲያ ደሳለኝ
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
