ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ2023/2024 በጀት አመት ከ4ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ አስታውቀዋል።
ከተገኘው ገቢም የባንኩ ትርፍ ታክስ ፤ከመጠባበቂያ እና ሌሎች ተቀናሾች በፊት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፉን ገልፀዋል።
ይህም ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር የ37 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሰዋል።
ባንኩ የተቀማጭ ሂሳቡን ወደ 4ቢሊዮን ብር በማሳደግ የተቀማጭ የገንዘብ መጠኑ ወደ 18.22 ቢሊዮን መድረሱን ተናግረዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው እንዳሉት ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የተከፈለ ካፒታሉን 2.48 ቢሊዮን ብር አድርሷል።
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ደግሞ ከ24 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አንስተዋል።
ባንኩ 73 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈት የቅርንጫፎቹ ብዛች ወደ 225 መድረሳቸው ተጠቅሷል ።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ታህሳስ 19 ቀን 2017 አ.ም በአድዋ ድልመታሰቢያ አዳራሽ 12 ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እንደሚያካሄድ ገልፀዋል ።
ሐመረ ፍሬው
ታኀሣሥ 18 ቀን 2017 ዓ.ም
