ማንችስተር ዩናይትድ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።
የኒውካስልን የማሸነፊያ ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ እና ጆኢሊንተን አስቆጥረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በውድድር ዘመኑ ዘጠነኛ የፕርሚየር ሊግ ሽንፈቱን አስተናግዷል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች በአንድ ወር ውስጥ አምስት የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ሲሸነፍ ከስልሳ ሁለት አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ቼልሲ ከኢፕስዊች ታውን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።
የኢፕስዊችን የማሸነፊያ ግቦች ዴላፕ እና ሁቺንሰን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ቼልሲዎች በተከታታይ ያደረጓቸውን ሁለት የፕርሚየር ሊግ መርሐግብሮች ተሸንፈዋል።
አስቶን ቪላ ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
