በኢትዮጵያ ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል ተባለ

በኢትዮጵያ ፋርማሲስቶች ማህበር የጠቅላላ ጉባዔ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ወርቁ በዳዳ ፤በኢትዮጵያ ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል።

ዶክተር ወርቁ ህገወጥ የአደንዛዥ እፅ መድኃኒት በተከታታይ ወደሀገር ውስጥ በድብቅ ሊገባ ሲል በኢትዮጵያ አየር መንገድና በጉሙሩክ ኮሚሽ ይያያዛል ብለዋል።

ዋነኛው ግን ምግብ እና መዳኒቲ ቁጥጥር ባለስልጣን ያልመዘገበው ሰባት የሚሆኑ የተለያዩ ከወባ መዳኒት ጋር የተያያዙ መዳኒቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተዘዋወሩ መያዛቸውን ገልፀዋል።

ይህም ከፍተኛ የሆነ የወባ ስርጭትን ተከትሎ ከወባ መዳኒት ጋር ተመሳስሎ የተሰራ መድሃኒት ሲዘዋወር ነበር ሲሉ ተናግረዋል ።

ምክትል የቦርድ ሰብሳቢው እነዚህ ህገወጥ መድኃኒትቶች በብዛት እየታዩ ያሉት በድሬዳዋ ፣ሀዋሳ ፣አርባምንጭና በጅማ ከተማ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

በውስጥ ለውስ መንገድም በቅርቡ በኮንቦልቻና መቀሌ መገኘቱ ችግሩን ውስብስብ እና አስቸጋሪ እያደረገው መምጣቱን አስረድተዋል።

እንደ ሀገር ጥናት አድርጎ ለመናገር ተቸግረናል ያሉት ዶ/ር ወርቁ፤ የባህርዳር ዩኒቨረሲቲ በቅርብ ጊዜ የወጡ የአፍሪካ ጥናቶችን ጨምቆ አውጥቷል ብለዋል።

ይህም 22.6 በመቶ ዝውውር እንዳለ ያመላክታል ነው ያሉት።

ልዑል ወልዴ

ታኀሣሦ 23 ቀን 2017 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *