በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ19ኛ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ በለንደን ደርቢ ብሬንትፎርድን የገጠመው አርሰናል 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለአርሰናል የማሸነፊያ ግቦቹን
ጋብሬል ሄሱስ ፣
ሚኬል ሜሪኖ እና
ጋብሬል ማርቲኔሊ ሲያስቆጥሩ
ለብሬንትፎርድ የማስተዘዛኛውን ግብ ብሪያን ምቡዬም አስቆጥሯል ፡፡
ብራዚላዊው የአርሰናል የፊት መስመር አጥቂ ጋብርል ጄሱስ ባለፉት አራት ጨዋታዎች ስድስት ግቦችን አስቆጥሯል።
ጁሪየን ቲምበር በጨዋታው ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ አርሰናል ቅዳሜ ከብራይተን ጋር የሚያደርገው ጨዋታ በቅጣት ምክንያት የሚያመልጠው ይሆናል።
መድፈኞቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ሊቨርፑል ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ማጥበብ ችለዋል።
ጋዲሳ መገርሳ
ታኀሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
