አዲሱን የፈረንጆች 2025 ዓመት ከ3ኛው ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላኑ ጋር በስኬት መቀበሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።
አየር መንገዱ ምቹ እና ዘመናዊ አውሮፕላኖችን ስራ ላይ በማዋል ለደንበኞቹ ምርጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል።
በአቪዬሽን መስክ በአፍሪካ ስኬታማ የሆነበትን መሪነት እና በዓለም ደርጃ ያለውን ተወዳዳሪነት አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገልጿል።
ታኅሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
