መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ተጎጂ የሆኑ ተመላሽ ዜጎች ተመልሰዉ ከመሄዳቸዉ በተጨማሪ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሌሎችንም ይዘዉ ይሄዳሉ ተብሏል፡፡
በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር መከላከል እና መቆጣጠር ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ፤ በ2014-15 መደበኛ ባልሆነ ፍልሰት ምክንያት ከተመለሱ 1መቶ33ሺህ ዜጎች ከ60ሺህ በላይ የሚሆኑትን ማግኘት እንዳልተቻለ አንስተዋል፡፡
በሴፍቲኔት ፕሮግራም ለማደራጀት ተሞክሮ የነበር ቢሆንም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት መገኘት እንዳልቻሉ ነዉ የተናገሩት፡፡
ከእነዚህ መሀል ግማሾቹ ወደ አከባቢያቸዉ ያልተመለሱ ፤ ግማሾቹ ደግሞ በለመዱት መንገድ የተመለሱ ዜጎች ነበሩ ብለዋል፡፡
በህገወጥ መንገድ ከአገር መዉጣት እንደ ባህል የተያዘባቸዉ አከባቢዎች አሉ የሚሉት አቶ ደረጄ፤ በእነዚህ አከባቢዎች የአገር ሽማግሌዎች ሳይቀር መርቀዉ ይሸኛሉ ብለዋል፡፡
በአንዳንድ አከባቢዎች ህገወጥ አዘዋዋሪዎች እና ደላሎች በማህበረሰቡ ዉስጥ ተሰሚነት ያላቸዉ ግለሰቦች መሆናቸዉን አንስተዉ፤ ለማህበረሰቡ ግንዛቤ መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እስከዳር ግርማ
ታኀሣሥ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
